Mulu Multimedia
2 min readSep 2, 2020

Challenge 10 Day 3 Answer By Lidiya Alemayehu

ገላትያ 1
ከ1-5
በዚህ ክፍል ውስጥ ጳውሎስ የእራሱን አገልግሎት ከእግዚአብሔር መሆኑን መመረጡን እየተናገረ ሰላምታ የሚያቀርብበት ክፍል ነው። ከዚህም ክፍል ቁ1ን ትኩረት በማድረግ አጥንቻለው።
ሐዋርያ: ማለት ሙሉ የውክልና ስልጣን ተሰቶት ለአንድ ተግባር የታላከ መልክተኛ ማለት ነው። ማለትም ቤተ ክርስቲያንን ለመትከል ለማጽናት ደግምም ለማሳደግ በባለቤትነት ሳይሆን ውክልና ተሰጥቶት የሚያገለግል አገልጋይ ነው። የቤተክርስትያን ባለቤት ክርስቶስ ነው። ስለዚህ ባሁን ዘመን የለን አገልጋዮች ስናገለግል ወይም የሐዋርያነት ጸጋ ሲኖረን እንደባለቤት ሳይሆን እንደ ክርስቶስ ተወካይ የተላከውን ፈፃሚ ሆነን በታማኝነት በትህትና ዝቅ በማለት ማገልገል ይኖርብናል።

ከ6-10
ይህ ክፍል ደግሞ የገላትያ አጠቃላይ መልክት ዋና ሀሳብን የያዘ ነው ማለትም የጽድቅን ሁኔታ የእውነተኛ ወንጌል ምንነት ያስረዳል። ጳውሎስ ቁ6 ላይ በክርስቶስ ፀጋ የጠራችሁን እርሱን ትታችሁ ወደ ተለየ ወንጌል እንዲህ መዞራችሁ ደንቆኛል ይላቸዋል። ይህም ሚያሳየው መጀመሪያ በፀጋ የጠራቸውን ወንጌል ምላሽ ሰተው ተረድተው እንደነበር ነገር ግን ከጊዜ በኋላ ወደ ተበረዘ ወንጌል መዞራቸውን ነው። እናም ወንጌል ወደ እኛ ድህነትን ጽድቅን ይዞ የመጣበት መንገድ እንዲያው በፀጋ ነው። አሁን እንኳን እራሳችንን ስመለከት ጥሩ ጥሩ ነገር ስናደርግ የምንጸድቅ ተቀባይነትን በዛ ያገኘን ይመስለናል። ምንም እንኳን በዛ ዘመን እንዳሉ የመገረዝ ያለመገረዝ ጥያቄ ባይኖርብንም የተሰጠን ጽድቅ ግን ከፀጋው እና በፀጋው ብቻ መሆኑን የማናስተውልበት ጊዜ ይኖራሉ ብዬ አስባለው። ነገር ግን የኛ ስራ ከንቱ ነው። (ትንቢተ ኢሳ 64:6 ላይ የኛ ጽድቅ የመርገም ጨርቅ ነው ይላል።) ማንም እንዳይመካ በስራ አይደለም እንዲሁ ነው።

ንፁህ ያልተበረዘ ወንጌል
*ሰው ሊጸድቅ የሚችለው እየሱስ ክርስቶስን በማመን ብቻ ነው።
*የሚቀደሰውም በክርስቶስ ፀጋ እና በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ነው።