mulu multimedia
2 min readJun 16, 2020

Day one challenge answer by Abriham Hilu

ለጥያቄዎቹ የተመለሰ በአብርሀም ሀይሉ

1 ጋብቻ ማለት በ ዘፍ 2፡21_24 ላይ እንደሚናገረው እግዚአብሄር አምላክ በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት አንቀላፍቶም ሳለ ከጎኑ አንዲት አጥንት ወስዶ ቦታውን በስጋ ሞላው። እግዚአብሄር አምላክ ከኣዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሰራት ወደ ዳምም አመጣለት።
እንዲሁም በኤፌሶን 5፡31_32 ላይ እንደሚለው ሰው እናቱንና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይሆናል ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ። ስለዚህ በሁለቱም ክፍሎች ላይ እንደተመለከትነው ጋብቻ ማለት......ሁለት ተቃራኒ ፆታ ያላቸው ሰዎች አንድ የሚሆኑበት ነው።

ማቴ 19፡6
ጋብቻ ማለት ከእጮኝነት ወደ ባልና ሚስትነት መሸጋገሪያ መንገድ ነው። ከመጋባታቸው በፊት ሁለቱ ወጣቶች ወይም እጮኛሞች በተለያየ ቤት የሚኖሩ፣ የየራሳቸው የኑሮ ዘይቤ የሚከተሉ፣ አልፎ አልፎ በመገናኝት የወደፊት ህይወታቸው እንዴት መምራት እንዳለባቸው ማውራትና እንዲሁም ልዩነቶቻቸውን አጥብበው በመተዋወቅ ላይ የሚያሳልፉት ጊዜ ነው። ነገር ግን ከተጋቡ ቡሀላ መፅሀፍ እንደሚለው ኤፌ 5፡31_32 አንድ ላይ መኖር ይጀምራሉ። ኑሯቸው አንድ የሚሆነው በስጋ ብቻ ሳይሆን በመንፈስም አንድ ይሆናሉ።

በሌላ መልኩ
ጋብቻ ማለት ስነ_ስራት ነው። ጋብቻ በስሩ ብዙ ነገሮችን ይዟል። ጋብቻ
የደስተኛ ወጣቶች ባልና ሚስት መሆናቸውን ብግልፅ የሚያሳይ ድርጊት ነው። የሚያመለክታቸውም ብዙ መሰረታዊ ነገሮች አሉት። እነርሱም

• አዲስ ቤት (መዝ 126፡1_5)
• አዲስ ጅማሬ (ዘፍ 2፡24)
• አዲስ ትሥሥር (ማቲ 19፡6)
• አዲስ ሀላፊነትና ሸክም (1ጢሞ 5፡8)
• አዲስ ድጋፍ/አጋር (መክ 4፡11᎐2)
• አዲስ ጉልበት (መክ 4፡11_12)
• አዲስ ደስታ (ምሳ 5፡18_23)
ምንጭ፡ የማገባው ማንን ነው
2 አንድ ጋብቻ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ጋብቻ ነው የምንለው በዘፍ 6፡2 እንደሚናገረው ወንዶች ልጆች ሴቶችን ውብ ሆነው አዩአቸው ስለሚል። እኛ ወንዶች የተፈቀደልን ወንድ ከሴት ጋር እና ሴት ከ ወንድ ጋር አንዲጋቡ እንጂ
ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት፣ ወንድ ከእንስሳ ወይም ሴት ከእንስሳ አይደለም። አልተፈቀደም። እነዚህ ነገሮች ፍጹም ከመፅሀፍ ቅዱስ ጋር የተፃረሩ ናቸው። እንደነዚህን ያለ ጋብቻ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም።

ሌላው መፅሀፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ጋብቻ የምንለው
• ከአንድ በላይ ሚስት ያለው ወይም ባል ያላት።
• ዝሙትና እርኩሰት ያላበት ጋብቻ።